ለማንቸስተር ዩናይትዱ ዋይኔ ሩኒ ቅዠት፥ ለባላጋራው የሊቨርፑሉ ሽቴፋን ዤራርድ ደግሞ ምርጥ ህልም ነበር ተብሎ
በመላ ብሪታንያ ተዘግቧል የትናንቱ ግጥሚያ። ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልትራፎርድ ስታዲየም የሊቨርፑልን ከባድ
ምት ቀምሷል። ጠንካራው ቸልሲ በአስቶን ቪላ ጉድ ሆኗል።
ቡንደስ ሊጋ፣ ላሊጋ እና ሴሪ ኣም ቅኝት ይደረግባቸዋል። ኢትዮጵያኖች በተሳተፉበት የኒውዮርኩ ማራቶን የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ባለድሉ ሞ ፋራህ ተዝለፍልፎ ወድቋል።በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የእግር ኳስ ግጥሚያ ሊቨርፑል ትናንት ማንቸስተር ዩናይትድን ጉድ አድርጎ ቸልሲን መጣሁብህ እያለው ነው። ሊቨርፑል አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ከቸልሲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት አራት ብቻ ለማድረግ ችሏል። በትናንቱ ግጥሚያ የሊቨርፑሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ሽቴፋን ዤራርድ የመጀመሪያዋን እና ቀጣዩዋን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። ቢጫ ካርድም አይቷል። የፕሬሚየር ሊጉን በ25 ከመረብ ያረፉ ግቦች በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ የሚገኘው ሉዊስ ሱዋሬዝ ሶስተኛዋን የማሳረጊያ ግብ ለሊቨርፑል ከመረብ አሳርፏል።
በትናንቱ ጨዋታ ሊቨርፑሎች አራት ቢጫ ካርዶች ሲመዘዝባቸው፤ በሜዳው ግብ ማስቆጠር ለተሳነው ማንቸስተር ዩናይትድ ግን የከፋ ነበር። ማንቸስተሮች ሁለት ቢጫ ካርድ ከተሰጣቸው በኋላ በ77ኛው ደቂቃ ላይ ኔማንያ ቪዲች የፕሬሚየር ሊጉ ሁለተኛ ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው ዳንኤል ስቱሪጅ ላይ ዳግመኛ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ዳንኤል ስቱሪጅ ለሊቨርፑል 18 ግቦችን በማስቆጠር ሶስተኛ ኮከብ ግብ አግቢ ከሆነው ከማንቸስተር ሲቲው ሠርጂዮ አጉዌሮ በሶስት ግቦች ከፍ ብሎ ይገኛል።
በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የትናንቱ ሁለተኛ ጨዋታ አርሰናል ቶትንሐምን 1 ለዜሮ መርታት ችሏል። ከትናንት በስትያ ደግሞ ማንቸስተር ሲቲ ሁል ሲቲን 2 ለባዶ፣ ሣውዝ ሀምፕተን ኖርዊችን 4 ለ2 ቀጥተዋል። ኤቨርተን ካርዲፍን 2 ለ1 ሲያሸንፍ፤ ፉልሐም ኒውካስልን 1 ለምንም አሰናብቷል። ዌስትሐም በስቶክ ሲቲ 3 ለ1 ሲረታ፤ ዌስት ብሮሚች ስዋንሲን 2 ለ1 ሸኝቷል። ሠንደርላንድና ክሪስታል ፓላስ ያለምንም ግብ ሲለያዩ፤ ጠንካራው ቸልሲ በአስቶን ቪላው ፋቢያን ዴልፍ ብቸኛ ግብ ጉድ ሆኗል።
ፕሬሚየር ሊጉን ቸልሲ በ66 ነጥቦች ሲመራ በሜዳው አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ሊቨርፑል በ62 ነጥብ ይከተለዋል። አርሰናልም አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ከሊቨርፑል ጋር ልዩነቱ የግብ ክፍያ ብቻ ነው። ሶስት ተስተካካይ ጨዋታዎች የሚቀሩት ማንቸስተር ሲቲ ከመሪው ቸልሲ ጋር ልዩነቱ የ6 ነጥቦች ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ48 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ እየተሰቃየ ይገኛል።
የማንቸስተር ዩናይትዱ ዝነኛው አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን የተኩት ዴቪድ ሞየስ የኦልትራፎርድ ቆይታቸው ከጠበቁት በላይ ከባድ እንደሆነ ከትናንቱ ሽንፈት በኋላ ገልጠዋል። እዛው ማንቸስተር ውስጥ አድጎ የጉርምስና ዘመኑን የጨረሰው ግልፍተኛው ዋይኔ ሩኒ በስፖርት ዓለም ቆይታዬ እንደትናንቱ የከፋ ቀን የለም ሲል በሊቨርፑል የደረሰባቸው የ3 ለባዶ ድቀት አሁንም ድረስ ያልለቀቀው «ቅዠት» እንደሆነበት ጠቅሷል።
ወደ ጀርመኑ ቡንደስ ሊጋ እናቅና። ኃያሉ ባየር ሙንሽን አሁንም በድል ጎዳና ለብቻው እየገሰገሰ ነው። በደረጃ ሠንጠረዡ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሌቨርኩሰንን ከትናንት በስትያ 1 ለባዶ አሸንፏል። ሔርታ በርሊን በሐኖቨር 3 ለዜሮ ተሸኝቷል። ስቱትጋርት ከ ቬርደር ብሬመን አንድ እኩል ወጥቶ ነጥብ ተጋርቷል። ትናንት ሐምቡርግ ኑረንበርግን 2 ለ1 ሲረታ፤ ፍራይቡርግ አይንትራኅት ፍራንክፉርትን በኮሜርስ ባንክ አሬና 4 ለ1 አርበትብቶ ጉድ አሰኝቷል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ቤተኛ ለመሆን ሦስት አሥርት ተጠብቆ ቢሳካም -ቀጥሎስ?
የደቡብ አፍሪካ ኢሊቨር ታምቦ ዓለም አቀፍ
አውሮፕላን ማረፊያ የደረስነው፣ የአፍሪካ አገሮች እግር ኳስ ዋንጫ (ቻን) ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያውን ጨዋታ በሊቢያ አቻው 2 ለ 0 በተሸነፈ ማግሥት ነበር፡፡
በደቡብ አፍሪካ በተለይም የአገሪቱ የንግድ ማዕከል
በሆነችው ጆሃንስበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወቅት የነበራቸው ስሜት አይስተዋልባቸውም፡፡
በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መለያ የለበሱ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በየአቅጣጫው መመልከት
የሚያስገርመውን ያህል አሁን ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ የደቡብ አፍሪካን ምድር በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወቅት ረግጠን ለነበርነው ሁሉ ሁኔታው አስገራሚም አጠያያቂም ነበር፡፡ ከምናነጋግራቸው ብዙዎቹ የመረጋጋት ስሜት የላቸውም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ጨዋታ ባልተጠበቀ ውጤት 2 ለ 0 በሊቢያ መሸነፏ ነው? ወይስ ተጨማሪ ምክንያት ይኖር ይሆን? የሚለውን ለማወቅ ጊዜ ማጥፋት ሳያስፈልግ አነጋግረናቸዋል፡፡ በጆሃንስበርግ በተለይም ኢትዮጵያውያን በሚንቀሳቀሱበት ጂፒ ስትሪት የወትሮው ዓይነት እንዳልሆነ ያስታውቃል፡፡ ከዋና ቤቶች ውጪ የነበሩ ሱቆችና ተያያዥ የንግድ መደብሮች ፈርሰውባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ለወትሮው በአዲስ ዓመት ዋዜማ ሞቅ ብሎ የሚጀመረው የንግድ እንቅስቃሴ ተዳክሟል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2013 የአፍሪካ ዋንጫና በ2014 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ተስፋ አድርገውበት የቆዩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደቡብ አፍሪካ አቻውን ከዓለም ዋንቻ ማጣሪያ እንዲሰናበት ምክንያት ሆኗል በሚል ደቡብ አፍሪካውያኑ ለኢትዮጵያውያኑ የነበራቸው አመለካከት እንደቀድሞው አለመሆኑን የሚናገሩት እነዚህ ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎች፣ ‹‹እዚህ እየተከናወነ ባለው የአፍሪካ አገሮች የእግር ኳስ ዋንጫ (ቻን) ላይ ቡድኑ ጥሩ ነገር ያሳየናል ብለን ጠብቀን ነበር፤›› ይላሉ፡፡ ምክንያቱም ከሻምፒዮናው በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዋንጫው ከተገመቱ ጥቂት ቡድኖች አንዱ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ የተጠበቀው ቡድን በተቃራኒ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
ተስፋ የተደረገበት እግር ኳስ መነሻ
ከሦስት አሥርት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የተቀላቀለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ለዚህ ታላቅ ስኬት የበቃው እያንዳንዳቸው የሚመለከታቸው አካላት ለእግር ኳሱ ቀጣይነት መሠረታዊ የሚባለውን ሥራ ሠርተው? ወይስ በአጋጣሚ? የሚለው ወትሮም ሲያነጋግር የነበረ መሆኑ አይካድም፡፡ ይኼው ጥያቄ ከአገር ቤት በባሰ ሁኔታ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተደጋግሞ ይነሳል፡፡ በተለይ ደግሞ በዋና አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው የሚመራው ቡድን አዳዲስ ልጆች ሊያገኝ አለመቻሉ፣ እውነት አሠልጣኙ እንደሚሉት በአገሪቱ ተተኪ ተጨዋቾች ጠፍተው ወይስ? የሚለው በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ጥያቄ ሆኖባቸዋል፡፡
ሐኪም ሁሴን የተባለ በደቡብ አፍሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ፣ ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ሁልጊዜ የምንጯጯኸው ነገሮች ከተበላሹ በኋላ ነው፡፡ እዚህ ደቡብ አፍሪካ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች የነበራቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ምን ይመስል እንደነበረ የምናስታውሰው ነው፡፡ ከተጨዋቾች አካል ብቃት ጀምሮ በርካታ ከፍተቶች ተመልክተናል፡፡ ይህንኑ በአገር ቤት የሚኖሩ ወገኖቻችን ያጡታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ምክንያቱም የሚታጨደው በተዘራው መጠን ነው፡፡ የተሻለ ምርት ለማግኘት በሠርገኛ መጣ ሁኔታ ሳይሆን በጥናት የተደገፈ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ እንደምንሰማውና እንደምናውቀው ከ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ማግሥት ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የነበረው ጠንካራና ደካማ ጎን ምን እንደሚመስል ጥናት ተደርጎ ለኅብረተሰቡ እንዳልተገለጸ ነው፡፡ ይኼ በሌለበት ምን ዓይነት የእግር ኳስ ውጤት ነው የምንጠብቀው? አሁንም ትርጉም ከሌለው ስሜታዊነት በመውጣት የዘመናዊ እግር ኳስ ግብዓቶች ምንድናቸው? እንዴትስ ወደ እዚያ መስመር መግባት እንችላለን? ያንን መስመር ሊያስጨብጡንና ሊያሲይዙን የሚችሉ ሙያተኞች እነማን ሊሆኑ ይገባል? የሚሉትን በጥልቀት በመመልከት ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል፤›› በማለት የአሁኑ ትርጉም የለሽ ጩኸት በሌለ ነገር ላይ መሆኑን ያስረዳል፡፡
ከአፍሪካ ዋንጫ በኋላ የኢትዮጵያ እግር ኳስን ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው እየተከታተሉ መሆናቸውን የሚናገሩ በርካታ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአቶ ሐኪምን አስተያየት ይጋራሉ፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የአፍሪካን እግር ኳስ ከመሠረቱ ጥቂት አገሮች አንዷ መሆኗ እየታወቀ፣ ነገር ግን ከአፍሪካ ዋንጫ ለሦስት አሥርት ዓመታት ያህል ርቃ ቆይታለች፡፡ አሁን ደግሞ ተመልሳ ቤተኛ ሆናለች፡፡ ወደ ቀድሞው ታሪክ አብሳሪነት ለመመለስ ጠንካራ ርብርብ ያስፈልጋል፡፡ ይኸው ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት እንዲደርስ ይጠይቃሉ፡፡
‹‹እግር ኳስ ከወቅታዊ ብቃት ጋር የሚገናኝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ነገር ግን ደግሞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከመጠን አልፎ ጎልቶ ይታያል፡፡ ምክንያቱም የአሠልጣኝ ሰውነት ቡድን ከሁለት ዓመት በላይ ቆይታ ባላቸው ተጨዋቾች የተዋቀረ ነው፡፡ ነገር ግን ደግሞ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴያቸው የተበታተነ በመሆኑ ያንን ለማቀናጀት ጊዜ የሚጠይቅ ነው፡፡ ከዚያም በላይ በብዙዎቹ ተጨዋቾች ላይ ግልጽ የሆነ የአቅም ችግር ይስተዋላል፡፡ አሠልጣኝ ሰውነት ዛሬ ‹‹በተተኪ›› የለም ሽፋን በልጆቹ ላይ እምነት እንደጣሉ ናቸው፤›› የሚሉት እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች፣ የአገሪቱ እግር ኳስ ባለቤት ካለው ይህንን አካሄድ አንድ ቦታ ላይ ማስቆም ይጠበቅበታል ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡
ዋና አሠልጣኝ ሰውነት ምን አሉ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሊቢያ አቻው 2 ለ 0 ከተሸነፈ በኋላ ለጋዜጣዊ መግለጫ ለቀረቡት አቶ ሰውነት ቢሻው ባልተጠበቀው ውጤት የተነሳ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ጋዜጠኞች፣ ‹‹ከአሠልጣኝነትዎ ይለቃሉ ወይስ ይቀጥላሉ?›› ሲሉ ላቀረቡላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ፣ ‹‹ከሚቀጥለው ጨዋታ በኋላ ውሳኔዬን አሳውቃችኋለሁ፤›› ብለው መናገራቸውን የተለያዩ ድረ ገጾች አስነብበዋል፡፡ በሁለተኛው ጨዋታ በኮንጎ 1 ለ 0 የተሸነፉት አሠልጣኝ አሁንም በተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ሥራ ፈት መሆን አልፈልግም፤›› በማለት በዋና አሠልጣኝነታቸው መቀጠል እንደሚፈልጉ ይፋ አድርገዋል፡፡
ይኼ የአሠልጣኙ ንግግር በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል፡፡ ይህንን መግለጫቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛውን ሽንፈት ባስተናገደበት ምሽት አሠልጣኙም ሆኑ ተጨዋቾቹ ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ በቦታው ለነበሩ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ ‹‹እባካችሁ ለአገሪቱ እግር ኳስና ለአገራችን ብሔራዊ ቡድን ስንል በደቡብ አፍሪካ ፖሊስና በደቡብ አፍሪካውያን ዜጎች እየደረሰብን ያለውን ዛቻና ማስፈራሪያ ችለን ለምንጮኸው ተመልካቾች አስቡልን፤›› ሲሉ ተማፅኖዋቸውን አሰምተዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ አሠልጣኙም ሆኑ ተጨዋቾቹ ያላቸው ስሜት ምን እንደሚመስል ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ አሠልጣኝ ሰውነት ይህንኑ አስመልክቶ ለሥራ ባልደረቦቻቸው ‹‹ሹክ›› ብለዋል እንደተባለው ከሆነ በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ከጨዋታው በኋላ አዲስ አበባ ካልሆነ በተናጠል መግለጫ የማይሰጡ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ዘገባ የተጠናቀረው የማክሰኞ ምሽቱ የኢትዮጵያና የጋና የመጨረሻው የማጣሪያ ጨዋታ ከመካሄዱ በፊት መሆኑን እየገለጽን፣ ለዚህ ዘጋቢ የደቡብ አፍሪካ ሙሉ ወጪ የሸፈነው በደሌ ስፔሻል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
በደረጀ ጠገናው፣ ከደቡብ አፍሪካ
ዘገባው የሪፖተር ጋዜጣ ነው
በቦክሲንግ
ደይ መጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሰዋንሲ ሲቲ ጋር ያደረጉት ሞሪኒሆ በጨዋታው ላይ ስዋንሲዎች እጅግ ፈታኞች ነበሩ፡፡
የእኔው ተጫዋቾች አስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ሲያስጨንቁኝ ቢቆዩም ሶስት ነጥብ ይዘን በመውጣታችን ደስ ብሎኛል
ብለዋል፡፡
ባለፈው ሣምንት የደረጃ ሰንጠረዡ መሪነታቸውን ለሊቨርፖል አስረክበው የነበሩት መድፈኞቹ ተመልሰው ወደ መሪነት በመመለሳቸው አሰልጣኝ አርሰን ቬንግር ይህ ቡድን በአሸናፊቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በምሽቱ ጨዋታ ላይ ልጆቼ ጥሩ በመጫወታቸው አሁን ወደ አሸናፊነት ከመመለሳችን ባለፈ የደረጃ ሰንጠረዡን ለመምራት የቻልንበት አጋጣሚ ተፈጥሯልም ብለዋል፡፡
በማንችስተር ሲቲ 2 ለ 1 የተሸነፉት የሊቨርፖሉ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ በእለቱ የመሃል ዳኝ የነበሩት ሌማንሰንን በእጅጉ ተችተዋል፡፡ ለውጤታቸው ማጣትም ተጠያቂው ዳኛው መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ውጤቱንም ለመቀበል የሚከብድ ነው ያሉት ብሬንዳ ሮጀርስ፣ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ ስተርሊንግ ያስቆጠረው ጎል ከጨዋታ ውጭ ነው በሚል መሻሩ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሊቨርፑል ለአንድ ሣምንት ከነበረበት የደረጃ ሰንጠረዥ መሪነት ወርዶ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ወደ
አሸናፊነት ከተመለሱ ወዲህ አምስተኛ ተከታታይ የአሸናፊነት ድላቸውን ማጣጣም የቻሉት የማንችስተር ዩናይትዱ ዴቪድ
ሞይስ ከ2 ለ 0 ተነስቶ 3 ለ 2 ማሸነፍ መቻል ትልቅ ፈተና ነው ፤ይህን ያደረጉት ተጫዋቾቼ ግን ጀግና ናቸው
በማለት ተጫዋቾቻቸውን አመስግነዋል፡፡
አሰልጣኙ እንዳሉት ከመሪዎቹ ጎራ ለመሰለፍ ረጅም ጊዜ ያስፈልገናል ለዚህም በየጨዋታው ነጥብ መሰብሰባችንን እንቀጥላለን በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በፕሪምየርሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ አርሰናል በ39 ነጥብ አንደኛ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ በ38፣ ቸልሲ በ37 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

Chan Africa 2014
በጉጉት የተጠበቀው የአርሰናል እና ቸልሲ ጨዋታ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 ተለያይተዋል፡፡
በሁለቱም ክለቦች ታሪክ 53ኛው አቻ እና በ10 ጨዋታ ግንኙነታቸው ሆዜ ሞሪንሆ በአርሰን ቬንገር ያለመሸነፍ ጎዞቸውን አስጠብቀው የወጡበት ጨዋታ ሆኗል፡፡
አሰልጣኝ ሞሪንሆ በታክቲክ የተመሰረተው አርሰናል ማሸነፍ እየፈለገላለመሸነፍ እያሰበ ቸልሲም ማሸነፍ እየፈለገ ላለመሸነፍ የተንቀሳቀሰበት በማለት በድፍረት ከማጥቃት ይበልጥ ጥንቃቄ ያየለበት ጨዋታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሰማያዊዎቹ በኩል ከእረፍት በፊት በፍራንክ ላምፓርድ አማካይነት ተገኝቶ የግብ ቋሚ የመለሰው አጋጣሚ የምታስቆጭ ነበረች፡፡
ከእረፍት መልስ ደግሞ አርሰናሎች በኦሊቨርድ ጅሩድ ሁለት ግሩም አጋጣሚዎች አምክኖ አርሰናል በመጨረሻው ሰዓት በአሸናፊነት የሚወጣበትን መልካም እድሎችን አበላሽቷል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በእኩል 36 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ መሪነቱን ለሊቨርፑል አስረክቦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ማንችስተር ሲቲ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ በ3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ቸልሲና ኤቨርተን በእኩል 34 ነጥን በግብ ክፍያ ተበላልጠው 4ኛ እና 5 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ