የደቡብ ሱዳን ሁኔታ ዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ እያሳሰበ ነው
በሁከቱ ቢያንስ ሃያ ስድስት ሰው መገደሉንና በሺኾች የሚቆጠሩ ሲቪሎች መፈናቀላቸውን የመንግሥቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የፖለቲካ ተቃዋሚያቸው ደጋፊዎች መፈንቅለ-መንግሥት ሞከሩብኝ ባሉ ማግሥትም ዛሬ በዋና ከተማይቱ ጁባ የተኩስ ልውውጡ ቀጥሎ ውሏል፡፡የጎረቤቶቿ የሱዳንና የኬንያ መሪዎችም ለሳልቫ ኪር ስልክ እየደወሉ አለኝታነታቸውን ገልፀውላቸዋል፡፡
የሱዳን መንግሥት “ሁኔታውን በቁጥጥር ሥር አውያለሁ” ካለ በኋላ ውጊያው መቀጠሉ ያሳሰባቸው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙንና የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናትም ገልፀዋል፡፡
ጎረቤቶቿ ሱዳንና ኬንያም እንዲሁ ሥጋታቸውን እየገለፁ ነው፡፡
ዘገባው የVOA ነው

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ